image
image
image
image
image

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ለስራ እድል ፈጠራ ዘርፉ የሚሆን የመስሪያ ቦታ ሼድ ግንባታ ተመረቀ፡፡

ግንቦት 14, 2018
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በዛሬው ዕለት ከተመረቁ 8 ትላልቅ ስኬቶች መካከል በኢኮኖሚው ዘርፍ ትልቅ ተስፋ የተጣለበትና የማህበረሰቡን የሥራ አጥነት ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ የታለመውን ስራ አንድ እርምጃ ወደፊት የሚያደርግ የመስሪያ ቦታ ሼድ ግንባታ ፕሮጀክት ተመርቋል። ለብዝዎቹ ወጣቶችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የሥራ ዕድል መፍጠሪያ የሚሆነው ይህ መስሪያ ቦታ በክፍለ ከተማው ወረዳ 03 ውስጥም መገኛውን አድርጓል። ይህ በ253 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈውና ለተደራጁ ማህበራት ሰፊ የመሥሪያ ቦታ አቅርቦትን ለማስፋፋት የተገነባው ዘመናዊ ሼድ በ21/07/2018 ዓ.ም. የተጀመረ እንደነበር ይታወሳል። መንግሥት ለዜጎች የሥራ ዕድል ፈጠራና ለኢኮኖሚ መነቃቃት የሰጠውን ከፍተኛ ትኩረት በሚያሳይ መልኩ ለዚህ ፕሮጀክት ማጠናቀቂያ በአጠቃላይ 10 ሚሊዮን 400 ሺህ ብር ወጪ ተደርጓል። ይህም የግንባታው ጥራትና ስፋት ለአምራችና ለአገልግሎት ሰጪ ማህበራት ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ታስቦ የተከናወነ መሆኑን ያረጋግጣል። የዚህ ፕሮጀክት በስኬት መጠናቀቅና ዛሬ ለምረቃ መብቃት ለከተማዋ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ዘርፈ ብዙ አበርክቶ እንዳለው ተገልጿል። በተለይም በሥራ አጥነት ለሚቸገሩ የማህበረሰቡ ክፍሎች አዲስ የሥራ በር የሚከፍት ከመሆኑም በላይ በተለያየ ሙያ ተደራጅተው ነገር ግን የመሥሪያና የማምረቻ ቦታ አጥተው ለነበሩ ማህበራት እጅግ አመቺና ስትራቴጂካዊ አማራጭ ይዞ መጥቷል። ይህም ክፍለ ከተማው አደራጅቷቸው ወደ ማምረት ለማስገባት እጥረት የሚገጥመውን የመስሪያ ቦታ ችግር በተወሰነ መልኩ የሚቀርፍ መሆኑንና የከተማዋን የንግድ እንቅስቃሴ እንዲያነቃቁ ትልቅ እገዛ እንደሚያደርግም ተነግሯል። በዛሬው ዕለት በተካሄደው ደማቅ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ዣንጥራር አባይ እና የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ምስክር ነጋሽ እንዲሁም የክፍለ ከተማው ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ዘመን ተስፋዬን ጨምሮ በየደረጃው ያሉ አመራሮች በተገኙበት ግንባታው በይፋ እንዲመረቅ ተደርጓል። ይህ ፕሮጀክት በክፍለ ከተማው እየተመዘገቡ ካሉ የልማት ስራዎች መካከል የከተማዋን ነዋሪዎች ሕይወት በቀጥታ የሚቀይርና የኢኮኖሚ ዋስትናን የሚያረጋግጥ ተጠቃሽ ተግባር እንደሆነ ተመላክቷል ።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች