ዜና | Oduu | News
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የሚገኙ የመስሪያ ቦታዎች የሀገርን ኢኮኖሚ በማጠናከር ረገድ ትልቅ ሚና እየተጫወቱ መሆናቸው ተገለጸ።

‎ከአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት እና ከክፍለ ከተማው ምክር ቤት የተውጣጡ የንግድ ኢንደስትሪና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በክፍለ ከተማው በሚገኙ የስራ ቦታዎች ላይ የመስክ ምልከታ አድርገዋል። ‎ ‎የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት የዜና ክፍል እንደዘገበው የጉብኝቱ ዋና ዓላማ የመስሪያ ቦታዎችን ያሉበት ሁኔታ እና በልማት እንቅስቃሴዎች ላይ ያላቸው ሚና ለመገምገም ነው። ‎ ‎የቋሚ ኮሚቴዎቹ አባላት በምልከታቸው ወቅት የመስሪያ ቦታዎቹ እያስመዘገቡ ያሉትን ዘርፈ ቡዙ አዎንታዊ ውጤቶች ተመልክተው መደሰታቸውን ገልጸዋል። ‎ ‎በክፍለ ከተማው የሚገኙ የመስሪያ ቦታዎች ለአካባቢው ነዋሪዎች ሰፊ የስራ ዕድል መፍጠራቸው በመስክ ምልከታው ወቅት የተገለጸ ሲሆን ተኪ ምርቶችን በማምረት የውጭ ምንዛሬን ማስቀረት ረገድም የሚጫወቱት ሚና ከፍተኛ ነውም ተብሏል። ‎ ‎በነዚሁ ተቋማት አማካኝነት ለአዳዲስ ሰራተኞች እና ለሌሎች ዜጎች ዕውቀትን ማሸጋገር መቻሉ እና ነዋሪዎች ከአካባቢያቸው ሳይርቁ እዚያው ተረጋግተው እንዲሰሩ በማገዝም ማህበራዊ መረጋጋት እንዲፈጠር ያስቻሉ ስለመሆናቸውም ከጉብኝቱ መረዳት ተችሏል። ‎ ‎በጉብኝቱ ወቅት የነባር የአዲስ እና በግንባታ ላይ ያሉ የመስሪያ ቦታዎች ሁኔታ ታይቷል። ‎ ‎ነባር የሆኑ መስሪያ ቦታዎች ለስራ ምቹ እና ጽዱ በማድረግ እና አዳዲስ የተገነቡ የመስሪያ ቦታዎች ደሞ ዘመናዊ አሰራርን የተከተሉ እና ምርታማነትን ለማሳደግ ታስበው የተገነቡ መሆናቸው የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የመስሪያ ቦታዎች ልማት ጽ/ቤት በጉብኝቱ ወቅት አሳውቋል። ‎ ‎የቋሚ ኮሚቴ አባላቱ በስተመጨረሻ እነዚህ ዘመናዊ የመስሪያ ቦታዎች ምርታማነትን በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ በሀገሪቱ አጠቃላይ ኢኮኖሚ ላይ ትልቅ እና ዘላቂ አስተዋጽዖ እንደሚኖራቸው ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። ‎የክፍለ ከተማው የመስሪያ ቦታዎች ልማት ጽ/ቤት በበኩሉ እነዚህን የመስሪያ ቦታዎች ለስራ ማመቻችትና ምርታማነትን በመጨመር የአገር ኢኮኖሚ ላይ የበኩላቸውን አስተዋ ማበርከት በሚችሉበት ደረጃ ለማድረስ እየሰራ እንደሚገኝ አስታውሶ በዚህም አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ እንደሚገኝ ጨምሮ ገልጿል። ‎

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ለስራ እድል ፈጠራ ዘርፉ የሚሆን የመስሪያ ቦታ ሼድ ግንባታ ተመረቀ፡፡

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በዛሬው ዕለት ከተመረቁ 8 ትላልቅ ስኬቶች መካከል በኢኮኖሚው ዘርፍ ትልቅ ተስፋ የተጣለበትና የማህበረሰቡን የሥራ አጥነት ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ የታለመውን ስራ አንድ እርምጃ ወደፊት የሚያደርግ የመስሪያ ቦታ ሼድ ግንባታ ፕሮጀክት ተመርቋል። ለብዝዎቹ ወጣቶችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የሥራ ዕድል መፍጠሪያ የሚሆነው ይህ መስሪያ ቦታ በክፍለ ከተማው ወረዳ 03 ውስጥም መገኛውን አድርጓል። ይህ በ253 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈውና ለተደራጁ ማህበራት ሰፊ የመሥሪያ ቦታ አቅርቦትን ለማስፋፋት የተገነባው ዘመናዊ ሼድ በ21/07/2018 ዓ.ም. የተጀመረ እንደነበር ይታወሳል። መንግሥት ለዜጎች የሥራ ዕድል ፈጠራና ለኢኮኖሚ መነቃቃት የሰጠውን ከፍተኛ ትኩረት በሚያሳይ መልኩ ለዚህ ፕሮጀክት ማጠናቀቂያ በአጠቃላይ 10 ሚሊዮን 400 ሺህ ብር ወጪ ተደርጓል። ይህም የግንባታው ጥራትና ስፋት ለአምራችና ለአገልግሎት ሰጪ ማህበራት ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ታስቦ የተከናወነ መሆኑን ያረጋግጣል። የዚህ ፕሮጀክት በስኬት መጠናቀቅና ዛሬ ለምረቃ መብቃት ለከተማዋ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ዘርፈ ብዙ አበርክቶ እንዳለው ተገልጿል። በተለይም በሥራ አጥነት ለሚቸገሩ የማህበረሰቡ ክፍሎች አዲስ የሥራ በር የሚከፍት ከመሆኑም በላይ በተለያየ ሙያ ተደራጅተው ነገር ግን የመሥሪያና የማምረቻ ቦታ አጥተው ለነበሩ ማህበራት እጅግ አመቺና ስትራቴጂካዊ አማራጭ ይዞ መጥቷል። ይህም ክፍለ ከተማው አደራጅቷቸው ወደ ማምረት ለማስገባት እጥረት የሚገጥመውን የመስሪያ ቦታ ችግር በተወሰነ መልኩ የሚቀርፍ መሆኑንና የከተማዋን የንግድ እንቅስቃሴ እንዲያነቃቁ ትልቅ እገዛ እንደሚያደርግም ተነግሯል። በዛሬው ዕለት በተካሄደው ደማቅ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ዣንጥራር አባይ እና የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ምስክር ነጋሽ እንዲሁም የክፍለ ከተማው ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ዘመን ተስፋዬን ጨምሮ በየደረጃው ያሉ አመራሮች በተገኙበት ግንባታው በይፋ እንዲመረቅ ተደርጓል። ይህ ፕሮጀክት በክፍለ ከተማው እየተመዘገቡ ካሉ የልማት ስራዎች መካከል የከተማዋን ነዋሪዎች ሕይወት በቀጥታ የሚቀይርና የኢኮኖሚ ዋስትናን የሚያረጋግጥ ተጠቃሽ ተግባር እንደሆነ ተመላክቷል ።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የውጭ ምንዛሬን በማስቀረትና የሀገር ኢኮኖሚ በማረጋጋት ረገድ በመስሪያ ቦታዎች የሚመረቱ ተኪ ምርቶች ሚና ከፍተኛ ነው ተባለ።

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የመስሪያ ቦታዎች ልማት ጽህፈት ቤት የምክር ቤት አባላት የመማክርት ጉባኤ፣ የሲቪክ ማህበራት እና የመስሪያ ቦታዎች የግቢ ኮሚቴ በጋራ በመሆን በክፍለ ከተማው በሚገኙ የማምረቻ ሼዶች ላይ የመስክ ምልከታ አደርገዋል። በጉብኝቱ በሼዶች ውስጥ የተሰማሩ አንቀሳቃሾች የሀገር ውስጥ ምርትን በመተካት ገበያን በማረጋጋት እና ሰፊ የስራ ዕድል በመፍጠር ረገድ ያላቸውን ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ተገልጿል። የመስሪያ ቦታዎች ልማት ፅ/ቤት ያስገነባቸውና እያስገነባቸው ያሉ የመስሪያ ቦታዎች ለአምራቾች ምቹ ሁኔታን የፈጠሩና ምርታማነትን በመጨመር በአገር ኢኮኖሚ ላይ አዎንታዊ ተጽዕኖ ያላቸው መሆኑ ከመስክ ምልከታው መረዳት ተችሏል። ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተሟላላቸውና ጽዳታቸው የጠበቁ እነዚህ የመስሪያ ቦታዎች በተቋሙ በሚደረግላቸው ተከታታይ ድጋፍ የካይዘን አተገባበር መሠረት አድርገው የሚሰሩ መሆናቸው ውብና ለስራ ምቹ እንዲሆኑ እንደሰዳቸውም መመልከት ተችሏል። የመስክ ምልከታው የአምራቾችን አቅም በመገምገም በሼዶች ውስጥ ያሉ ማህበራትና ኢንተርፕራይዞች ያሉባቸውን የስራ እንቅስቃሴና የስራ ቦታ አጠቃቀም በመመልከት ችግሮችን ለመፍታት በመስሪያ ቦታዎች በኩል ያሉ የመሰረተ ልማትና የአሰራር ክፍተቶችን ለይቶ ድጋፍ እና ክትትል ለማድረግ ያለመ እንደሆነ ተቋሙ ገልጿል። በባለ ድርሻ አካላትና በአምራቾች መካከል ቀጥተኛ የሃሳብ ልውውጥ በማድረግ ያሉ ክፍተቶችን ለመሙላት እንደዚህ አይነት የመስክ ጉብኝቶች ሚና የላቀ እንደሆነም ተሳታፊ ባለ ድርሻ አካላትና አምራቾች ሀሳብ ሰጥተዋል። ተኪ ምርቶችን በማምረት ረገድ የተመዘገቡ ስኬቶች በጉብኝቱ ወቅት የተብራሩ ሲሆን በበርካታ ኢንተርፕራይዞች ከዚህ ቀደም ከውጭ ሀገር በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ይገቡ የነበሩ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት መተካት እንደተቻለም ተገልጿል። የውጭ ምንዛሬን ከማዳን አኳያም በአልባሳት፣ በቆዳ ውጤቶች፣ በጽዳት መጠበቂያ ግብዓቶችና በምግብ ማቀነባበር ዘርፍ የተሰማሩ አምራቾች የገቢ ምርቶችን በከፍተኛ ደረጃ እየተኩ እንደሆነ መገንዘባቸው የጉብኝቱ ተሳታፊዎች አስረድተዋል። በሌላ መልኩ የገበያ ዋጋን በማረጋጋት ምርቶችን በቀጥታ ከአምራች ወደ ሸማች እንዲደርስ በማድረግ የኑሮ ውድነቱንና የገበያ መናጋቱን ለመቀነስ የጎላ አስተዋጽኦ እያበረከቱ እንደሆነም ነው የተገለጸው። የሀገር ውስጥ ምርቶች ከውጭ ከሚገቡት እኩል ተወዳዳሪ በመሆን በተለያዩ ተቋማት ስራ ላይ ውለው በተግባር ታይቷል ያሉት አምራቾቹ የጥራት የመለዋወጫ እና የባለሙያ ግብዓት በራስ አቅም በሚሸፈን መንግስት በዘረፉ የያዘውን አላማ በማሳካት ላይ መሆናቸውን አስረድቷል። ይህ በክፍለ ከተማው የተዘረጋው የመስሪያ ቦታዎች ልማት ለአካባቢው ወጣቶችና ሴቶች አዲስ ተስፋ የፈነጠቀ መሆኑ በጉብኝቱ ወቅት ለማስተዋል ተችሏል። በሼዶቹ አማካኝነት በሺዎች ለሚቆጠሩ ስራ አጥ ወጣቶች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ ዕድል ከመፍጠሩ ባሻገር የቴክኖሎጂና ክህሎት ሽግግር በማድረግ ወጣቶች በተግባር የታገዘ የስራ ላይ ስልጠና አግኝተው ራሳቸውን እንዲችሉ አግዟልም ተብሏል። ኢንተርፕራይዞች ከማሸጋገር አንጻር እንደ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ብቁና ተወዳዳሪ የሆኑ ስድስት ኢንተርፕራይዞች ከጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ(ዶክተር) በገላን ጉራ የኢንዱስትሪ መንደር 1ሺ 300 ካሬ በመረከብ ወደ አምራች ኢንዱስትሪነት ማደጋቸውም ከጉብኝቱ ገለጻ ማወቅ ተችሏል። በጉብኝቱ የተሳተፉ ባለድርሻ አካላት በበኩላቸው ከአምራቾች ለተነሱላቸው የገበያ ትስስርና ሌሎች ክፍተቶች ለመፍታት ከሚመለከታቸው የከተማው አስተዳደር አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል። የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የመስሪያ ቦታዎች ልማት ጽህፈት ቤት ያመቻቻቸው እነዚህ ሼዶች የሀገርን ምርታማነት በማሳደግና የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ረገድ ያላቸው ሚና ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ማለቱና ለዚህም አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ከወትሮው በተሻለ በመስራት ላይ እንደሚገኝ መግለጹን የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት የዜና ክፍል ዘግቧል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የቂርቆስ ክ/ከተማ መስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት የ6 ወር እቅድ አፈፃፀሙን ከባለድርሻ አካላት ጋር ገመገመ፡፡

በግምገማው ወቅት የጽ/ቤቱ ሃላፊ ወ/ሮ ፍፁም እንደገለፁት ባለፉት 6 ወራት በመስሪያ ቦታ አሰጣጥ ለበርካታ ሴቶች፤ወጣቶችና አካል ጉዳተኞች ቅድሚያ በመስጠት ተጠቃሚ እንዲሆኑ መደረጉን ገልፀዋል፡፡ የውይይቱም ተሳታፊዎች በበኩላቸዉ እንደገለፁት ፅ/ቤቱ ምቹ የስራ አካባቢ በመፍጠር አገልግሎቱን ማሻሻል መቻሉ እና በተቋም ደረጃ በቴክኖሎጂ ተደግፈው የሚሠጡ አገልግሎቶች የላቀ ውጤት መመዝገቡን በመግለፅ ቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አንስተዋል። በመጨረሻም በ6 ወሩ የተሻለ አፈፃፀም ላሳዩ አካላት እዉቅና ተሰጥቷል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
ቂርቆስ ክ/ከተማ መስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት ባለሙያዎችና አመራሮች በ2017/18 በክረምት ወቅት የተተከሉ ችግኞችን ውሃ የማጠጣት እና ሌቾች የእንክብካቤ ስራዎችን አከናወኑ።

ቂርቆስ ክ/ከተማ መስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት ሃላፊ በችግኝ እንክብካቤ መርሃ ግብሩ ላይ እንደተናገሩት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የመተባበርና የአንድነት ውጤት ማሳያ መሆኑን ገልጸው የሚተከሉ ችግኞች የአየር ንብረት ለውጡን ከመከላከል ባሻገር ለከተማው ውበት የሚሰጡና ለምግብነት የሚውሉ በመሆናቸው መትከል ብቻውን ውጤት ባለመሆኑ የተተከሉ ችግኞችን መንከባከብ የሁላችንም ሃላፊነት ሊሆን ይገባል ብለዋል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
በስታንዳርድ አመዘጋገብ ዙሪያ ለባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ።

በቂርቆስ ክ/ከተማ መስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት በስታንዳርድ አመዘጋገብ ዙሪያ ለባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
ወርቃማዋ ሰኞ ሳምንታዊ የሰራተኞች ማነቃቅያ ፕሮገራም ተካሄደ።

በቂርቆስ ክ/ከተማ መስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት በሳምንቱ ሁሉም አመራሮችና ሰራተኞች የሚሳተፉበት እጅግ አስተማሪ የሆነ የወርቃማ ሰኞ ፕሮግራም ተካሄደ። በማነቃቂያ መርሀ-ግብሩ ሁሉም የጽ/ ቤቱ ሰራተኞች ተገኝተውበታል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ለ100 ኢንተርፕራይዞች እና ለ329 አንቀሳቃሾች የመስሪያ ቦታ ቁልፍ ርክክብ አካሄደ፡፡

ክፍለ ከተማው በዛሬው እለት የስራ እድል ለተፈጠረላቸው 100 የሚሆኑ ኢንተርፕራይዞችን እና በውስጣቸው የሚገኙ 329 አንቀሳቃሾችን ቁልፍ አስረክቧል። የእድሉ ተጠቃሚ ለሆኑት ዜጎች የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክታቸውን ያስተላለፉት የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ምስክር ነጋሽ እንደተናገሩት መንግስት ለዜጎች ካለው የላቀ ክብር የስራ እድል በመፍጠር ብቁ ዜጋ እያፈራ ይገኛል ብለዋል። መንግስት ለዜጋው በተለይ ለስራ ፈላጊው ወገን ተቆርቁሮ የስራ እድል በመፍጠርና በማመቻቸት በሀገራችን ቀዳሚው የለውጥ አመራር ነው ያሉት ዶክተር ምስክር ከዚህም አኳያ ከሰባት አመት ወዲህ በየአመቱ በየክፍለ ከተማው፣ በየወረዳው፣ በየብሎኩ ያሉ የስራ እድል ያልተፈጠረላቸው ዜጎች በማኑፋክቸር፣ በኢንዱስትሪ፣ በአገልግሎት፣ በከተማ ግብርና በተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ተቀጥረው እንዲሰሩ እንዲሁም በሁሉም ዘርፍ በመለየትና በመመዝገብ በቴክኒክ እና በልዩ ልዩ ስልጠናዎች ከቴክኒክና ሙያና ከሌሎች ተቋማት ጋር በመቀናጀት ስልጠና በመስጠት በማብቃት ወደስራ ከመግባታቸው በፊት ግንዛቤ እንዲይዙ ማድረግ ቀጥሎ ደግሞ መስሪያ ቦታ እና ሼዶችን እንዲሁም የተለያዩ ኢንተርፕራይዞችን በማመቻቸት ምቹ ሁኔታ እየፈጠረ ይገኛል ብለዋል፡፡ የተፈጠረላቹ የስራ እድል እናንተን፣ ቤተሰቦቻችንን ከመጥቀም አልፎ ለሀገር ጭምር የሚያበረክተው አሰተዋጽኦ ከፍተኛ ነው እናንተም ስራን ሳትንቁ ስራን አክብራቹ በተፈጠረላቹ የስራ እድል በመጠቀም የስራ እድል ላላገኙ ወገኖች ጭምር የስራ እድል ለመፍጠር በርትታቹ እንድትሰሩ ሲሉም መልእክታቸውን አስተላፈዋል፡፡ በክፍለ ከተማው 199 ብሎኮች አሉ፤በእነዚህ ብሎኮች ላይ ምርታማነትን ከመጨመር፣ ስራ ከመፍጠር አኳያ ለበርካታ ዜጎች በስራ እድል ፈጠራ ላይ የሰራንበት ሁኔታ ነው ያለው ያሉት ደግሞ በክፍለ ከተማው ምክትል ስራ አስፈጻሚና የስራ ክህሎት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዘመን ተስፋዬ ናቸው። መስሪያ መሸጫ ቦታ መስጠት ብቻ አይደለም የእኛ ሀላፊነት በቅርበት መከታተል፣ የገበያ ትስስር መፍጠር፣ የክህሎት ክፍተት ካለም ሞልተን በተለይ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠቃሚ ሁናችሁ በአካባቢያችሁ ኢኮኖሚ ላይ ተጽዕኖ እንድትፈጥሩ ለማድረግ ከጎናችሁ ነን ሲሉም አቶ ዘመን መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
ጽ/ቤታችን በ6ወር አፈጻጸም ምዘና የላቀ አፈጻጸም በማምጣት ከ10 ክ/ከተሞ 2ኛ በመውጣት የእውቅና ሰርተፍኬት ማግኘት ችሏል፡፡

እንኳን ደስ ያለን ጽ/ቤታችን በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ በ6ወር አፈጻጸም ምዘና የላቀ አፈጻጸም በማምጣት ከ10 ክ/ከተሞ 2ኛ በመውጣት የእውቅና ሰርተፍኬት ማግኘት ችሏል፡፡

image
image
image
image